ደብዳቤ ለአዛውንት ዜጋ

 

English عربيه русский עברית Português Español Français


ውድ አረጋውያን(አዛውንት) ዜጎች ሰላም ለእናነት ይሁን!

 

እኛ የስራ፣ ማህበራዊ ጉዳይና የማህበረሰብ አገልግሎት ሰጭ ቢሮ ሰራተኞች ወደ እናንተ የምናቀርበው ጥሪ ቢኖር እርዳታ በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ እኛ እናንተን ለማገዝ ዝግጁዎች መሆናችን እንገልጻለን፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከቤታችሁ መውጣት ከሌለባችሁና የእኛ እርዳታ ካስፈለጋችሁ ከጎናችሁ ነን፡፡

ይህ ወቅት በጣም ፈታኝና አስቸጋሪ ወቅት ነው፡፡

በዚህ ጊዜ እናንተን እንዴት መርዳት እንዳለብን ማወቅ እንፈልጋለን፡፡

እርዳታ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ወደ እኛ በስልክ ቁጥር 118 በመደወል ወይም በምትኖሩበት ከተማ በሚገኘው አገልግሎት ሰጭ ስልክ ቁጥር 106 በመደወል እርዳታ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

በተጨማሪም ከታች በሚዘረዘሩ መረጃዎች አማካኝነት የስልክ መልዕክት መላክ ትችላላችሁ፡፡

በዚህ አጋጣሚ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዛሬ ጥቅምት 1 ቀን 2020ዓ/ም ጀምሮ እየተከበረ ላለው ዓለም አቀፍ የአረጋውያን(አዛውንቶች) ቀን በሰላም አደረሳችሁ እንላለን፡፡ አዲሱ ዓመትም የሰላም፣ የፍቅርና ጤና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞታችን እንገልጻለን፡፡

እኛ የማህበራዊ ጉዳይ ሰራተኞች እዚህ ያለነው እናንተን ለማገልግለ ነው፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በዚህ ዓመት ለተፈጠሩ ችግሮች አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብና የእናንተን የተለየ ችግር ለመስማትና መፍትሄ ለመፈለግ ዝግጁዎች ነን፡፡

ለእናንተ ጥሩ የተባለውን አገልግሎት ለመስጠት እንቀሳቀሳለን፡፡

Back To Top