ስለ አጠቃቀሙ ሁኔታ

Publication date: 21/03/2020, 14:24 | Update date: 20/05/2020, 09:33

ስለ አጠቃቀሙ ሁኔታ

አጠቃላ

አገረ እስራኤል  በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት አማካኝነት ይህንን የአፕሊኬሽን አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ ነች። ይህንን አገልግሎት ሰታቀርብ የተለያዪ  የአጠቃቀም ቅድመ ሁኔታዎች ደንቦችና የግላዊ መግለጫ ላይ የተመሰረተ ይሆናል።  እነዚህ ደንቦች አልፎ አልፎ እንዳስፈላጊነቱ የግላዊ መግለጫ  ሊቀያየሩ ይችላሉ። ማንኛውም ተጠቃሚ በየጊዜው የአጠቃቀሙን ውል በእጁ ስልክ ላይ ባለው አፕሊኬሽን በሚቀበለው በመልክቶች አማካኝነት  ፍቃደኝነቱን ያሳውቃል ። ፍቃደኛ ካልሆነም  ግን አፕሊኬሽኑን  በመፋቅ(በመሰረዝ) እስከ አሁን የተቀበላቸው መረጃዎች ይሰረዛ።

የዚህ አፕሊኬሽን የአጠቃቀም ግላዊ መግለጫ ተግባራዊ የሚሆነው የአፕሊኬሽኑ ውል መሠረት በአፕሊኬሽኑ መጠቀም ከጀመሩበት  ቀንና ሰዓት ጀምሮ ይሆናል::

"ተጠቃሚ" የሚለው አባባል የሚያመለክተው ማንኛውም ሰው አፕሊኬሽኑን በእጅ ስልኩ  በመጫን የአገልግሎት ተጠቃሚ የሆነ ሁሉ ነው::

የአፕሊኬሽኑ " አገልግሎት ከዚህ ቀጥሎ በተጠቀሰው መሰረት መጠቀም የተከለከለ ነው ፤ ለመጥፎ ነገር ፤ ተጠቃሚው "በአፕሊኬሽኑ " መገልገል የሚችለው ለሕጋዊ አጠቃቀም ብቻ ነው ።

ጤና ጥበቃ መ/ቤት ባለው መብቱ መሰረት "የአፕሊኬሽኑን" አገልግሎቱንና የመጠቀሙን ሁኔታ ለማቋረጥ ይችላል ፤ የጤና ጥበቃ መ/ቤት ወይም ሌላ ባለመብት የሆነ አጠቃቀሙ ከአግባቡ ውጭ መሆኑን መርምሮ ከደረሰበት  "የአፕሊኬሽኑን " አገልግሎት ያቋርጠዋል ።

የአገልግሎቱ ዋና ዓላማ

"በአፕሊኬሽኑ" ሁለት ዓይነት አገልግሎቶችን  መቀበል ይቻላል፣

  1. ለተጠቃሚዎች - ስለሁኔታው ሰፊ መረጃን ለመሰብሰብ "አፕሊኬሽኑ " የተጠቃሚዎችን እንቅስቃሴዎች ጤና ጥበቃ ሚ/ር መ/ቤት በበሽታው የተያዙት ሰዎችን መረጃ በማጣመር ይመረምራል:: በምርመራው ተጠቃሚው ከኮሮና ሕመምተኞች ጋር የተነካካ ወይም ለቫይረሱ መጋለጡን ያሳውቃል::
  2. "አፕሊኬሽኑ" ተጠቃሚዉን ድንገት ለቫይረሱ ተጋልጦ ከሆነ ከመጋለጡ 14 ቀናት በፊት የነበረባቸውን ቦታዎች፣ ቀናትና ሰዓት እነዲያስታውስ ይረዳዋል:: ይህ ለሕዝብ የሚደረገውን ቅድመ ማሳወቂያ  አስፈላጊነት መሰረት፣ ከታማሚው አካባቢ የነበሩትንና የተነካኩትን ሰዎች ፣ሰዓቶችንና ቦታዎችን በመግለጥ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግ ነው ከእሱ ጋር ንክኪ የነበራቸውና በኮሮና የተያዙ በሽተኞችን ማግኘት እንዲችል ለጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት መርዳት ይሆናል።  በዚህ ሁኔታ የተጋለጡት ሰዎችም ወደ ልዩ ልዩ መገለያ ቦታዎች እንዲገቡ ለማስቻል ይረዳል::

ሊተኮርበተ የሚገባ ነጥብ - በ"አፕሊኬሽኑ" የተገኘውን መረጃ ከጤና ጥበቃ ሚ/ር መ/ቤት በሌሎች የመገናኛ አውታሮች ወይም ሜድያ የሚተላለፉትን መረጃዎችና መመሪያዎች አያጣጥልም::

"አፕሊኬሽኑ" በጤና ጥበቃ መ/ቤት የተገኙ መረጃዎችና መመሪያዎች መካከል መጣጣም ከሌለ፣ ጤና ጥበቃ የሰጠው መመሪያ በበላይነት ተቀባይነት ይኖረዋል። በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የታለመለት አገልግሎት በአጠቃላይ፣ ተጠቃሚዎች በኮሮና ከታመሙ ሰዎች ጋር ንክኪ እንዳላቸው አስቀድሞ እንዲታወቅ ለመርዳት ነው ።

ቦታ

"አፕሊኬሽኑ"የሚጠቀመው ተገልጋዩ ሰው የደረሰባቸውን ቦታዎችና ሰዓቶች ዘርዝሮ በማሳወቅ፣ የእንቅስቃሴውን ታሪክ ለመግለጥ ነው። (ይኸውም " መረጃው ") ይባላል። የሚሰበሰበው መረጃ የግድ ፣ተጠቃሚው የመረጃዎችን ቁምነገር ለመረዳት እንዲያስችለውና ዓላማዉን ተግባራዊ  ለማድረግ እንዲችል ነው።  በአጠቃላይ ተጠቃሚው "ከአፕሊኬሽ" የሚቀበለው አገልግሎት ከላይ የተጠቀሰውን መረጃ ማግኘት እንዲያስችለው ነው።

በአፕሊኬሽኑ የተሰበሰበውን መረጃ፣ በእጅ ስልክ ላይ በሚገኘው አፕሊኬሽን ውስጥ   ከተጫንበት ጊዜ ጀምሮ ይከማቻል እንጅ፣ ከዚያ በፊት አይደለም ። ነገር ግን ተጠቃሚው ሰው "ጉግል" የመረጃ ማህደር ውስጥ ያለውን ከ14 ቀናት ወደኋላ በነበረባቸው ቦታዎች ዝርዝር ታሪክ ለመጠቀሚያ ፈቃኛነቱን በግልፅና በዝርዝ ከሰጠ ብቻ የሚደረግ ይሆናል ። ይህም  በእጅ ስልክ ላይ የቦታ መጥቀሻ አማራጩ እንዲሰራ በማድረግ ነው ፤

መረጃው የሚጠቀሙ  ይህን አፕሊኬሽን ከመጫንህ በፊት ከታመሙ ሰዎች  መረጃዎች ጋር ለማጣጣም ወይም ለማነፃፀር ነው ።

ስለመረጃው አጠቃቀም

የተሰበሰበው መረጃ በተጠቃሚው ሰው የእጅ ስልኩ ውስጣዊ ማስታወሻ ላይ ብቻ ነው የሚቀረው:: መረጃው በጤና ጥበቃ መ/ቤት ወይም ወደ ሌላ አካል አይላክም፤

ተጠቃሚው ለኮሮና ቫይረስ ከተጋለጠ  እሱ ወይም ተወካዩ የተሰበሰበውን መረጃ ወደ ጤና ጥበቃ መ/ቤት ለማስተላለፍ እንዲፈቅዱ ይጠየቃሉ:ይህም የተጋለጡ ሰዎችን ለማግኘትና

በፍጥረት ወደ መገለያ ቦታ እንዲገቡ ለማሳወቅ::አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለህብረሰቡ ማሳወቅና ማሰራጨት፣ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት በዚህ መረጃ መጠቀም የሚችለው በተሰጠው የግላዊ መግለጫ መሰረት ይሆናል::

ግዴታንና ሐላፊነትን ስለመገደብ

ጤና ጥበቃ መ/ቤት " አፕሊኬሽኑ " እንዳለ ለአገልግሎት ያቀርባል (AS IS ) ፤

ጤና ጥበቃ መ/ቤት " አፕሊኬሽኑ " ቢበላሽና ወይም ቢጠፋ ወይም ከመመሪያው ውጭ በሆነ አጠቃቀም ለዚህ( ኃላፊነትን አይወስድም ) ወይም በተጠቃሚው በግሉና በመብቱ በመፈጸም  ምክንያት ለሚፈጠር ችግር ኃላፊነት አይወስድም  ። ይህም የተቃራኒ አጠቃቀም ጉድለት ፤ የቴክኖሎጅውን አጠቃቀም ችሎታ በማጣት ቢበላሽ ወይም በማንኛውም ሌላ ምክንያቶች ለሚደርሰው ችግር ኃላፊነት የለበትም ።

ጤና ጥበቃ መ/ቤት አቅሙ በሚፈቅደው መጠን የ "አፕሊኬሽኑን "  አገልግሎቱን  የተስተካከለ ቋሚነቱንና  ደህንነቱን ለመጠበቅ በተቻለ መጠን ይጥራል።

ሆኖም ግን "አፕሊኬሽኑ" አዲስ እንደመሆኑ መጠን ከአስቸኳይ ፍላጎት በተሟላ ሁኔታ አገልግሎት መስጠተ ያዳግታል::    

ለተጠቃሚው ቋሚና ጥራት ያለው አገልግሎት ያለማቋረጥ ለመስጠትና  ያለ ምንም ስህተት ለማቅረብ፣ ፍጹም የሆነ ዋስትና ለመውሰድ አይቻልም ። እንዲሁም መሥሪያ ቤቱ ግዴታውን ወይም ኃላፊነቱን የሚወስደው የሚያጋጥመውን መሰናክል ለማስተካከልና ጉድለቱን ፍጥነቱን  ለሟሟላት ብቻ ነው ።

ከዚህ ጋር  "አፕሊኬሽኑ ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ላይ በሚደርሰው ጉዳት ወይም " "አፕሊኬሽኑ " የተጫነበት የእጅ ስልክ ወይም ከመመሪያው በተቃራኒ፣ በተደረገ አጠቃቀም ለሚደረሰው ችግር መሥሪያ ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም ።

የኮሮና በሽታ ለተያዘ በሽተኛ መያዙን በ"አፕሊኬሽኑ "አይነገርም ፣ የሚነገረው በባለሙያ ሀኪም ብቻ ይሆናል ። ተጠቃሚው በኮሮና በሽታ ስለመጋለጡ  በ"አፕሊኬሽኑ " መልክት

ሲደርሰው፣ ለተጋለጠው የሚመከረው ፤ ለዚህ ሁኔታ የተጋለጠባቸውን ቦታዎችና ጊዜዎች ለማሳወቅ የመሥሪያ ቤቱ የኢንተርኔት ድረ-ገጽ በሚወጣው መግለጫ ላይ ብቻ ነው ።

በ"አፕሊኬሽኑ"  የሚቀርበው መረጃ መሠረቱ በሪፖርቶች ነው ። ከፊሎች በሌሎች ተጠቃሚዎች ስልክ ከተቀመጡት መረጃዎች ናቸው ፤ ስለዚህ በትክክለኝንታቸው ላይ ጉድለት ሊኖር ይችል ይሆናል ፤ ወይም በከፊል መረጃው ብቻ ወይም እንዲያውም ጭራሹን የተሳሳቱም ሊሆኑ ይችላሉ ። ይህም በቴክኖሎጅ ስህተት  ምክንያት ሊሆን ይችላል ፤

ስለዚህ መሥሪያ ቤቱ በተጠቃሚዎች ስምምነት ስለመረጃው ትክክለኝነት ጉዳይ ኃላፊነትን አይወስድም ፤ በመሆኑም ተጠቃሚው ቃል የሚገባውና የሚስማማው በዚህ አገልግሎት ምክንያት መሥሪያ ቤቱን የሚቃወም አቤቱታ ወይም ክስ ያለበት ማመልከቻ ማቅረብ እንደማይኖርበት ወይም እንደሌለበት ነው ።

ይህን መሳይ ችግር ወይም ገደብ ግላዊ መግለጫ መኖሩን አውቆ ፣ በአገልግሎቱ መጠቀም እንዳለበት ነው። መረጃው የሚጠራቀመው በግሉ በስልኩ  ብቻ እንደመሆኑ መጠን፣ ለተጠቃሚው ምንም ዓይነት የጥርጣሬና አቤቱታ ሊኖረው አይገባም። ይህ በእንዲ እንዳለ ተገልጋዩ በፍቃዱ በመተግበሪያው አማካኝነት ያስተላለፈው መረጃ ዙሪያ የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤትን ምንም አይነት ጥያቄ ሊጠይቅና በኀላፊነት ሊጠይቅ አይችልም::  

ይህን ክፍል በተመለከተ - ይህም ማለት ፤ " የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት " በአብዛኛው መ/ቤቱን ፤ ሰራተኞቹን ፤ ተወካዮቹንና ለእርሱ አገልግሎት የሚያቀርቡትንም ሁሉ ማለት ነው ።

ስለ መተግበሪያው "አፕሊኬሽ ለውጦች "

ጤና ጥበቃ ሚስቴር መ/ቤት መብቱን ለእርሱ ፣ ለግሉ ብቻ የሆነውን ያስጠብቃል ፤ " አፕሊኬሽኑ " ሙሉ ለሙሉ ለማስወገድ ወይም ለመገደብ ጊዜ ወይም አገነባቡን ወይም ቅርጹን ፣በይዘቱ ለውጦችን ወይም አገልግሎቶቹን ፤ ይህም የሚያትተው የአጠቃቀሙን ሁኔታ፣  ስለለወጦች አዲስ ማስታዎቂያና  መግለጫ በመስጠት ሲሆን፣ ተጠቃሚው "

አፕሊኬሽኑ " ከስልኩ ማንሳት ወይም ማስወገድ እንዲችል ጭምር ይሆናል ።

" አፕሊኬሽኑ " ሲወገድ የተከማቸው መረጃም አብሮ ይሰረዛል ወይም ይጠፋል ።

* ለተጠቃሚው፣ ከላይ እንደተገልጠው፣ በለውጦች የተነሳ ፣  መሥሪያ ቤቱን  በሚመለከት ምንም ዓይነት አቤቱታ ወይም ተቃውሞ ወይም  ክስ  የማቅረብ መብት  አይኖረውም።

ስለግል አጠቃቀም ብቻ ገደቦች

" አፕሊኬሽኑ" አጠቃቀምና አገልግሎት ለግላዊ ህጋዊ ዓላማው ብቻ  ነው ። ይህም ከላይ ከተገለፀው  ዝርዝር ገደብ ባልወጣ መልኩ ብቻ ነው"። ይህም አፕሊኬሽኑን ለንግድና ህጋዊ ላልሆነ መጥፎ ተግባር መጠቀም ክልክል ሲሆን በተጨማሪም የአፕሊኬሽኑን ስራ ለማዛባት ወይም በአፕሊኬሽኑ የሚገኙትን መረጃዎች ማሰናከል ክልክል ነው::

" በአፕሊኬሽኑ " ልዩ ምልክት ከ"አፕሊኬሽኑ " አጠቃቀም ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት በሌለው ሁኔታ መጠቀም ክልክል ነው ።  በልዩ ምልክቱ ለመጥፎ  ዓላማ መጠቀም ፤ በአንቀጽ 5 በ 1947 ዓ.ም በወጣው ሕግ የወጣውን፣ የልዩ ምልክቶች ጠባቂ  ሕግ መሰረት በወንጀል ያስቀጣል ።

Back To Top