ይህ ሀመጌን የተባለው አፕሊኬሽን የተሰራው በእስራኤል ሀገር በግል ከሚሰሩ ባለሙያዎችና በጤና ጥበቃ መ/ቤ የሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ነው ።
በማንኛውም ሰዓት ( አሁን፤ በየሰዓቱ ) ይህ አፕሊኬሽን በጤና ጥበቃ መ/ቤት የሚገኙ መረጃዎችን ያወርዳል ፤ እነዚህ መረጃዎችም በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሕሙማን (በጤና ጥበቃ መ/ቤት የኢፕድሚኖሎጂ ምርመራና ጥናት የተደርገባቸው ሰዎች::) የነበሩበትንና የሄዱበት የመንገድ መስመሮች ያሳያል ( ቀናቶችንና ሰዓቶችን ያጠቃልላል ) ። ይህንን መረጃ ከአንተ የእጅ ስልክ ከሚገኘው የቦታ ዝውውር ጋር በአንተው የእጅ ስልክ
ላይ ብቻ ያጣምረዋል ።
ይህ መረጃም፤ በአናን (ከኮምፒውተሩ ውጭ መረጃን መጠበቂያ ) አይቀመጥም ። ለቫየረሱ ከተጋለጠ ሰው ጋር በአንድ ቦታ እንደነበረ የመልዕክት መረጃ ከደረሰበው ፤ መረጃው ወደ የጤና ጥበቃ መ/ቤት አይተላለፍም ነገር ግን የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት መረጃውን ወስዶ በንክኪ የተጠረጠሩትን ሰዎች ወደ ጊዜያዊ ማቆያ ለማስገባት እንዲረዳው ከፈቀድክ ብቻ ይሆናል፤ አፕሊኬሽኑ እራሱ ከየት ቦታና በስንት ሰዓት ከበሽተኛው ጋር አብራችሁ እንደነበራችሁ የፅሁፍ መልክት ይላክልሃል ።
ይህን የፅሁፍ መልክት ከተቀበልክ በኋላ ፤በአስቸዃይ ወደ ጤና ጥበቃ የኢንተርኔት ድር-ገጽ በመግባት በቫይረሱ የተያዙ ሕሙማን የነበሩባቸውን ቦታዎችና ሰዓቶችን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ፤ አፕሊኬሽኑ በሰጠህ መረጃ ጥርጣሬ ካለህ ፤ የጤና ጥበቃ መ/ቤት መረጃ መቀበያ *5400 መደወል፣
ወደ ማጌን ድቫዲ አዶም በመደወል ወይም ለኩፓት ሆሊም (የሕክምና ክሊኒክ) በመደወል የመረጃ መቀበልና መመካከር ትችላለህ ።
ይህ መረጃ የተሰባሰበው ከእስራኤል ውስጥ የኢፕዲምኖሎጅያዊ ጥናትእና ከተለያዩ ላብራቶሪዎች ብቻ ሲሆን አፕሊኬሽኑን ካዘጋጀው የጤና ጥበቃ መ/ቤት ተወካይ የዲጊታላዊ ፊርሚያን (ሀቲማ ዲጊታሊ) ያዘለ ይሆናል ።በተቻለን መጠን ክትትል በማድረግ የተላከው መረጃ ከጤና ጥበቃ መ/ቤት መሆኑ ማረጋገጥና የተለያዩ አደገኛ የሆኑ ፕሮግራሞች እንዳይገቡበት በጥብቅ ክትትል እናደርጋለን ፤
የተለያዩ አደገኛ ፕሮግራሞች አፕሊኬሽኑን ከፍተው ለመግባት ብዙ ጥረት የሚያደጉ እንዳሉ እናውቃለን ፤ ስለዚህ በተቻለን መጠን ቁጥጥር በማድረግ ማንነትክን ለመጠበቅ እየሰራን እንገኛለን ፤
የሚካሄደው (ኢንተርኔት በሌለብት) ExpressRoute ተብሎ በሚጠራልዩ መንገድ ነው ፤
ውስጥ የተጠበቀውን የጉዞ ታሪክ (እንቅስቃሴ) ለጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት በማሳተፍ በንክኪ
ምክንያት በቫይረስ ሊጋለጡ የሚችሉትን በየኢፒዲሚዮሎጂ የምርመራ ጥናት ቶሎ በማግኘት
እርዳታ ለመስጠት ነው::
መረጃው ወደ ጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት እንዲተላለፍ ከፈቀደ በሁለት ዓይነት መንገድ ይካሄዳል
የመጀመሪያው ለተገልጋዩ የማመልከቻ ሊንክ መረጃውን ለማስተላለፍ ፍቃዱን የሚያረጋግጥበት
ሊንክ ይላክለታል:: በሁለተኛ ደረጃ ተገልጋዩ መረጃውን ለጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ለማስተላለፍ
በመተግበሪያው (አፕሊኬሽን) አማካኝነት ይፈቃዳል::
የኢፒዲሚዮሎጂ የምርመራ ጥናት ይገመገማል ተገልጋዩ ፍቃድ የሰጠባችው ከጉዞ ታሪክ ጋር
ግንኙነት ያላቸው መረጃዎች ለኢፒዲሚዮሎጂ የምርመራ ጥናት እንዲያገለግሉ በመጠበቅ
የተገልጋዩን የማንነት ሚስጢር በመጠበቅ ለህብረተሰቡ አስፈላጊ የሆነው መረጃ ይሰራጫል
ይህም ተገልጋዩ በነበረባቸው ቦታዎች የነበሩ ሰዎችንና የመተግበሪያው ተጠዋሚዎችን ለማሳወቅና
ለማስጠንቀቅ ይሆናል፣ እነዚህ የተጠቀሱት ቦታዎች በጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ድህረ ገፅ እና
የኮሮናን ስርጭተ በሚያሳየው ካረታ(ማፕ) ይፋይሆናል:: ቦታዎቹም የኮሮና በሽተኞች የጉዞ ታሪክ
በመባል ወደ መተግበሪያው ይመለሳል::
በጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት ለ7 ዓመታት ያህል ይጠበቃል፣ እሱም ከኢፒዲሚዮሎጂ የምርመራ
ጥናት የማጣራት ሁኔታ ጋር ግንኙነት የሌላቸው መረጃዎችን ያጠቃልላል
ሌሎች ለኢፒዲሚዮሎጂ የምርመራ ጥናት ያላገለገሉ ስብስብ መረጃዎች ወደ በጤና ጥበቃመስሪያ ቤት ከተላለፉ 30 ቀናት በኋላ መረጃውም መረጃው የተላለፈበት መንገድ
ይሰረዛሉ(ይፋቃ ሉ)፣ በእነዚ ጊዜያት የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት በተሰበሰበው መረጃ በተሻሻለ
የቴክኖሎጂ ምርመራ በመጠቀም ለኮሮና ቫይረስ የተጋለጡ በሽተኞችን ለማግኘት የጠቀምበታል::
መረጃ በሚስጥራዊ ኮድ ይተላለፋል፣ይህ መረጃም የግላዊና ሚስጢራዊነቱን በመጠበቅ ሁኔታ
በጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት የመረጃ ማስቀመጫ (ማቆያ) የኢንተርኔት ማዕከል (ሻራት) የበሽተኞችን
የግል ሚስጥር በሚጠብቀው ህግ መሰረት ይጠብቀዋል::
በየ ጊዜው ይመረምራል፣ እንዳስፈላጊነቱም የጥበቃ ማሻሻያ ያደርጋል::
በቅርቡ በ GitHub አማካኝነት የመጀመሪያውን ኮድ ይፋ ልናደርግ ዝግጅት ላይ እንገኛለን ፤ ይፋ የምናደርገውም ሁሉንም መረጃ ሲሆን (የተለያዩ የግብይት መረጃዎች ግን ዝግ ይሆናሉ)
የሃገር አቀፍ ደህንነት አስጠባቂ መስሪያቤት ጨምሮ ይህ አፕሊኬሽን የተለያዩ የታዎቁ ባለሙያዎች ምርመራ አድርገውለታል ፤ በግል የሚሰሩ አዋቂ ባለሙያዎች ፤ በእስራኤል የሚገኙ የኮንፒውተርን መረጃ የመጠበቅ ባለሙያዎች የሆኑ የድርጅት ሰራተኞች ሳይቀሩ ምርመራ አድርገውለታል ፤ ይህም ምርመራ የሚያካትተው ፤ የግንባታ ዲዛይኖች ፤ የኮድ ምርመራ (የክፍተት ምርመራ) በተሰጡት መረጃዎች መሰረት ያሉትን ስህተቶች ማስተካከል ፤ ይህን አፕሊኬሽን ለህብረተሰቡ ጥቅብ በጣም ምቹና ማንኛውም የኮንፒውተር መርጃ ሰራቂ ሰው የማይገባበት መሆኑና ጥሩ ነው ብለን እናምናለን ፤ይህ አፕሊኬሽን ለተጠቃሚዎች ባቀድነው ዓላማ መሰረት መጠቀም እንችላለን ፤
አስፈላጊውን ጥረት ብናደርግም ፤ ያለንን የስራ ልምድ ተመክተን ክትትል ብናደርግም ፤ መቶ በምቶ ፐርሰንት የተዘጋጋ ቴክኖሎጅ የለም ፤ ስለዚህ ፤ አንድም የመርጃ መስረቅ ችግር ከደረሰ ፤ ተጠቃሚዎችን በአስቸኳን እናሳውቃቸዋለን ፤ ይህንም የምናደርገው አስፈላጊውን መከታ ለማድረግ እንዲያስችለን ሲባል ነው ፤