የኮሮና ቫይረስ መረጃ

Русский | العربية | English | עברית

ስለ ኮሮናን ቫይረስ በሽታንና በበሽታው ምክኒያት እቤት መገለልን አስመለከቶ ጥያቄ ካለዎ "ሞኬድ ኮል አብሪውት" በ *5400 / 08-6241010 (ከ 8፡00 እስከ 23፡00) በመደዎል ለጥያቄዎ መልስ በአማርኛ ቋንቋ ይቀበላሉ፡፡ 


በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሰጡ መግለጫዎች / መምሪያዎች

 

በእስራኤል የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መስፋፋትን ለማቆም የህብረተሰቡ ከቦታ ወደ ቦታ እንቅስቃሴ ለመቀነስ ከዛሬ እሮብ 25/03/2020 ከ17፡00ሰዓት ጀምሮ መንግስት አዳዲስ መመሪያዎችን በይፋ አፅድቋል:: የበለጠ ለመረዳት >

ከጤና ጥበቃ ሚ/ ር የተሰጠ ማስታዎቂያ ፦ ወደ ሽርሽር ቦታዎች መሄድ ተከልክሏል ፤ ወደ ትልልቅ የገቢያ ቦታዎች ( ኬንዮኖች) መሄድ ተከልክሏል ፤ ወደ ባሕር አካባቢ ለሽር ሽር መሄድ ተከልክሏል ። የበለጠ ለመረዳት >

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተሰጡ መግለጫዎች / መምሪያዎች ። የበለጠ ለመረዳት >

የኢፕዲሚኖሎጅክ ጥናቶችን አሰባስቦ ለሕዝብ በኢንተርኔት ድረ- ገጹ ላይ ይፋ ማድረግ የሚችለው የጤና ጥበቃ መ/ቤት ብቻ ነው ። የበለጠ ለመረዳት >

የህዝብ ማስታወቂይ
የኢፒደሚዎሎጅያዊ (የተላላፊ በሽታዎችን ክትትልና መከላከል) የመረመራውን ሂደት ለማፋጠን የቴክኖሎጅ ዘዴ መጠቀም ጀምረናል ። የበለጠ ለመረዳት >

የጤና ጥበቃ ሚንሰተር መ/ቤት የሰጠው መግለጫ
ከቤት መውጣት የተከለከለ ነው ። የበለጠ ለመረዳት >

 


ኮል ሀብሪኡት የስልክ አገልግሎት

 

ለሞኬድ ኮል ሀብሪኡት ለጤና ድምፅ ድረ ገፅ እዚህ ላይ የጫኑ

 

በተጨማሪ አሙታት "ጤና ብሪኡት" እና አሙታት "ፊደል" የስልክ አገልግሎት ይሰጣሉ

טנא בריאות        פידל

04-6323544                        054-3331230

 

የኮሮና ወረርሽኝ በሽታ መከላከያ - የስልክ አገልግሎት
የ " ጤና ብሪኡት " ጤና አጠባበቅ ድርጅት ለኢትዮጵያዊያን ማሕበረሰብ የኮሮና ወረርሽኝን በሽታ ሁኔታ በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎችና መግለጫዎችን ለመስጠት አስቸኳይ የስልክ አገልግሎት ከፍቷል ።
በዚህ አገልግሎት ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ለሚፈልጉ ሁሉ ፤ ስለ ወረርሽኙ የመከላከያ እርምጃዎች ማስረጃ ለሚፈልጉ ሁሉ ፤ ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መ/ቤት የሚሰጡ የተለያዩ መግለጫዎችና መምሪያዎች ለመከታተል ለሚፈልጉ ሁሉ አስቸኳይ የስልክ አገልግሎት መስጠት ጀምረናል ።
መግለጫውን የሚሰጡት ዶ/ር ሰፈፈ በላይ አይቸህ ናቸው በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ ከ 08፡00-21፡00 ባሉት ሰዓቶች አገልግሎቱ ይካሄዳል ።

 

የፊደል ድርጅት ስለ ኮሮና ቫይረስ መከላከል ከጤና ጥበቃ ሚንስቴር የሚሰጠውን መመርያ ወደ አማርኛ፣ ዕብራይጥና ትግርኛ ቋንቋዎች ቃል በቃል በመተርጎም ከዕሁድ እስከ ሐሙስ ባሉት የሳምንቱ ቀናት ከ12፡00 እስከ 19፡00 ሰዓት በተንቀሳቃሽ ስ/ቁጥር 054-3331230 አገልግሎቱን ያበረክታል።ማሳሰቢያ፦ ይህ የስልክ አገልግሎት በሐኪሞችና በጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሚሰጡት ሕክምና ምትክ እንዳልሆ ግን ከወዲሁ እንገልፃለን።


የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የወቅቱ ዓለምን ዕረፍት የነሳው የወረርሽኝ በሽታ አጠቃላይ መግለጫ

 

"የኮሮና ወረርሽኝ " በሽታ ካለፈው ከዲጼምበር ወር 2019 ዓ.ም ጀምሮ በቻይና አገር ውስጥ በመከሰቱና አዲስ በሽታ ሆኖ በመገኘቱ በዓለም ላይ ከፍ ያለ ስጋትን በመፍጠር ላይ ይገኛል ። 

ይህ በሽታ ውሎ ሳያድር ስርጭቱ በፍጥነት በመዛመት፣ ይህ ጽሑፍ እስከ ወጣበት ቀን ድረስ በዓለማችን ከ 90 በላይ አገሮችን የበከለ መሆኑ እየተገለጠ ይገኛል ።

የኮሮና ቫይረስ ማንነትና የወረርሽኙ መስፋፋት ሁኔታ
ኮሮና ቫይረስ በዚህ በቤተስብ ስሙ ይጠራ እንጅ በውስጡ ልዩ ልዩ ዝርያዎችን የያዘና ከላይኛው መተንፈሻ አካል ጀምሮ ወደታች በመውረድ በሳንባ ላይ ከፍ ያለ በሽታን በማባባስ የሚጎዳና እስከ ሞት አደጋም የሚያድርስ ነው ። ቫይረሱ ስሙን ያገኘው ከአካሉ ቅርጽ ነው ፤ ይህም ማለት በላቲን ቋንቋ " ኮሮና " ማለት " ሆሎ " ወይንም " ክራውን - ዘውድ " ማለት ሲሆን፣ የቫይረሱ ውጫዊ አካል የዘውድ ቅርጽ እንዳለው መስሎ ስለሚታይ ነው ።የኮሮና ቫይረስ እስከ አሁን ቢያስ ሶስት ታዋቂ ዝርያቶች አሉት ፦
1ኛ . የመካከለኛው ምሥራቅ የመተንፈሻ አካል ሕመም መነሻ ፤ሜርስ (MERS-COV)
2ኛ . የከባድና የአጣዳፊ የመተንፈሻ አካል ሕመም መነሻ ፤ ሳርስ (SARS-COV)
3ኛ . የዛሬው የአዲሱ ወረርሽኝ በሽታ መነሻ ናቸው ፤ኖብል ኮሮና (nCOV)
ይህ ቫይረስ የሚያጠቃው በዋናነት የመተንፈሻ አካልን (ጉሮሮን ፤ ሳንባን ) ነው ። በተነጻጻሪነት ሲወዳደር ፣ ይህ ቫይረስ መጠኑ ትልቅ፣ ጠባዩ በሞቃት የአየር ጠባይ በቀላሉ የሚጠቃ ፤ ተላላፊነቱ በሳልና በንጥሻ ጠብታዎችና እጅ ለእጅ የመጨባበጥ ሁኔታ ዋና መንገዶች ናቸው ።

የበለጠ ለመረዳት >


በኮሮና ቫይረስ በሽታ ተጠርጥረው ለ14 ቀናቶች በቤት ውስጥ ለሚገለሉ ሰዎች የተሰጡ 14 መመሪያዎች !!

 

1. ከእቤት መውጣት ፈፅሞ የተከለከለ ነው

2. አየር በሚነፍስበት በአንድ ክፍል ውስጥ ይገለሉ

3. እጅዎን በሳሙና እና በውሃ በተደጋጋሚ ይታጠቡ

4. ቢቻል ከሌላው ቤተሰብ ለየት ያለ የመጸዳጃ ክፍል ይጠቀሙ

5. በሚያስነጥስዎ ወይም በሚያስልዎ ጊዜ በሶፍት ይጠቀሙ

6. በቤት ውስጥ የሚገኙት ሰዎች አነስቸኛ መሆን አለባቸው

7. አስታማሚ ወይም ጠያቂ ወደ ተገለሉበት ክፍል ማስገባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው

8. እሚገለሉበት ክፍል በቂ አየር እንዲኖረው መስኮቶችን መከፋፈት አስፈላጊ ነው

9. ጭምብል (የአፍ መሸፈኛ ወይም መሃርም) በመጠቀም አካባቢዎን ይጠብቁ

10. ቆሻሻዎችን ለየት ባለ እቃ ውስጥ ይጣሉ::

11. የተጠቀሙበትን ልብስ ለየት ባለ ማከማቻ በማስቀመጥ ለብቻ ማጠብ።

12. የመመገቢያ ቁሳቁሶችን  በጋራ አይጠቀሙ

13. የሚኖሩበትን ክፍል በየቀኑ ያፅዱ

14. የህመም ስሜት ከተሰማዎት ወደ አምቡላንስ የጥሪ ማዕከል 101 በስልክ መስመር ይደውሉ


ዶ/ር ዳኒኤል ረዳይ የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምንድነው


ዶ/ር ስፈፈ በላይ አይቸው የኮሮና ቫይረስ በሽታ ህብረተሰቡ ሊያደርጋቸው የሚገባው ጥንቃቄ

ከምንወዳቸው ሰዎች በመራቅ ህይዎታቸውን እናድን

 

ከቤታችን አንወጣም
ከቤት የሚወጣባቸውና የማይወጣባቸው ጉዳዬች

 

 

דיווח בידוד לחוזרים מחו"ל

 Home isolation report for international travelers

דיווח בידוד לחוזרים מחו"ל

 Home isolation report after contact with a COVID-19 case 

דיווח בידוד לחוזרים מחו"ל

 Report a violation of the home isolation duty

Back To Top